Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ ወጣቶችን በስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው-አቶ ሀምዲ ሰላህዲን

ሀረር፣ጥቅምት 24/2018(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል ወጣቶችን በስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀምዲ ሰላህዲን ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ከሀረር ብድርና ቁጠባ አ.ማ ጋር በጋራ በመሆን የ2018 በጀት አመት አንደኛ ሩብ ዓመት የብድር ስርጭትና አመላለስ አፈጻጸምን የወረዳ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገምግሟል።

የሀረሪ ክልል ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀምዲ ሰላህዲን እንደገለፁት በክልሉ የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመረውን ጥረት ለማሳካት ለስራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ተሰጥቷል።

ወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማስቻል በተሰራው ስራ ባለፉት 3 ወራት ብቻ 25 ሚሊየን ብር ብድር ማቅረብ መቻሉን ገልፀዋል።

ወጣቱን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራው ስራ ወጣቶች ስልጠና እንዲያገኙ ከማድረግ ጀምሮ የመስሪያ ቦታ መሰጠቱንም አክለዋል።

የሚሰጡ የገንዘብ ብድሮች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ከማድረግ አኳያም የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ግብረሀይል በማቋቋም እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ባለፉት 3 ወራት 13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ብድር ማስመለስ መቻሉን ጠቁመዋል።

በቀጣይም ከብድር ስርጭትና አመላለስ ጋር ተያይዘው እያጋጠሙ የሚገኙ ችግሮችን በመቅረፍ ወጣቱን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish