Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ ከ7 ሺ 3 መቶ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል-የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ 

ሀረር ሚያዚያ 8/2017(ሀክመኮ):-በሐረሪ ክልል ከ7 ሺ 3 መቶ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸውን የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም ገለፁ። 

የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በአምስት ሚሊየን ኮደርስ መርሀ ግብር ስልጠና ከ 7 ሺ 3 መቶ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል። 

የኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም የኮደርስ ስልጠናው የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት በማዳበር እንደ ሀገር የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለማሳለጥ እንደሚያግዝ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል። 

እስካሁን በኢኒሼቲቩ በተሰራው ስራ በክልል ደረጃ ስልጠናውን ካጠናቀቁ ወጣቶች መካከል 3 ሺህ የሚሆኑት የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ጠቁመዋል። 

በመርሀ ግብሩ ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አንድሮይድና ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙም ገልጸዋል። 

ሥልጠናው ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት ከማድረግ ባለፈ፣ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል። 

ስልጠናው ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል በሆኑ ስልጠናውን ያልወሰዱ በቀጣይ ግዜያት ተመዝግበው እንዲሰለጥኑ ሀላፊው ጥሪ አስተላልፈዋል። 

በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከ9 ሺህ በላይ  ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱንም አቶ ጀማል ኢብራሂም ገልጸዋል።https://ethiocoders.et/

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish