Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ ባለፉት 3 ወራት ከ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 32 ባለሀብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ተሰጥቷል-አቶ ሀምዲ ሰላህዲን

ሀረር፣ጥቅምት 23/2018(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል
ባለፉት 3 ወራት ከ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 32 ባለሀብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀምዲ ሰላህዲን ገለፁ።

ከለውጡ ወዲህ በክልሉ የኢንቨስትመንት ዘርፍ መነቃቃት መፈጠሩን የገለፁት አቶ ሀምዲ ሰላህዲን
የክልሉ መንግስት በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚሰማሩ አልሚዎች አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በተለይ በኢንቨስትመንት ዘርፉ የነበሩ ማነቆዎችን ለመፈታት ትኩረት ተሰጥቶ በተሰራው ስራ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ይህም በዘርፉ ለሚሰማሩ አልሚዎች ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።

የክልሉ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ተከትሎ ከግዜ ግዜ በክልሉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚሰማሩ አልሚዎች ቁጥር እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል።

በክልሉ የሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶችን ለክልሉ ኢኮ ኖሚ ብሎም ለዜጎች ከሚያበረክቱት ጥቅም አንፃር በመለየት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።

በዚህም ባለፉት 3 ወራት ብቻ ከ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 32 አልሚዎች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን ነው አቶ ሀምዲ ሰላህዲን የገለፁት።

ፍታድ የተሰጣቸው በኢንዱስትሪ፣ሆቴልና በሌሎች ዘርፎች ለሚሰማሩ አልሚዎች መሆኑንም ገልፀዋል።

የኢንዱስትሪ ዘርፉ ያለንን ሀብትና የሰው ኃይል በመጠቀም የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ፣ተኪ ምርቶችን በማምረት አበረታች ውጤት የተመዘገበበት መሆኑንም ገልፀዋል።

በኢንዱስትሪው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው መሻሻል ዘርፉ የክልሉን ኢኮኖሚ ለማጠናከር የሚያደርገውን አስተዋፅኦ በተግባር እያሳየ እንደሚገኝም አቶ ሀምዲ ሰላህዲን ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish