Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት በጤናው ዘርፍ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

ሐረር፤የካቲት 19/2017(ሐክመኮ):-በሐረሪ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን በማረጋገጥ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በዛሬው ዕለት መካሄድ በጀመረው የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት በጤናው ዘርፍ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውንም ባቀረቡት ሪፖርት አንስተዋል።

በክልሉ በሚገኙ የጤና ተቋማት ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 4 መቶ 62 ሺ 913 ዜጎች በተመላላሽ ህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውንም በማሳያነት አቅርበዋል።

ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና በማከም ረገድም አበረታች ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ባለፉት 6 ወራት በወባ በሽታ ምክንያት አንድም ሞት አለመመዝገቡን ለተመዘገበው ውጤት በማሳያነት ጠቅሰዋል።

በተለይ ለእናቶችና ህፃናት ጤና፤ለማህፀን በር ካንሰር፣ ለስኳርና ደም ግፊት ህመሞች የቅድመ ምርመራና ህክምና ስራዎች በትኩረት ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።

የጤና አገልግሎቱን ይበልጥ ለማሰለጥም በተሰራው ስራ የጤና መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት ረገድ ሁለት ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማጠቀቅ መቻሉን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከስነ ምግባር እና አሠራር ጋር ተያይዘው ይስተዋሉ የነበሩ ተግዳራቶችን በመፍታት ለማህበረሰቡ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች ተሰርተዋል።

በተለይ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ከህክምና ግብአትና የመድሀኒት አቅርቦት ጋር ተያይዘው ይነሱ የነበሩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ርብርብ መደረጉን አክለዋል።

ማህበረሰቡ የተሟላ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ከማስቻል ባለፈም የሀረር ከተማን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገልፀዋል።

የግሉ የጤና ዘርፍም በዚህ ረገድ ሚናውን እንዲወጣ ተገቢ አመራር እየተሰጠ እንደሆነ ጠቁመዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish