በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የተሰሩ ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸው ተገለጸ።
በሀረሪ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የተሰሩ ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ገልጸዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሮዛ ኡመር በቢሮው ባለፍት ስድስት ወራት በተከናወኑ ተግባራት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በክልሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የኑሮ ውድነቱን ለማርገብ በትኩረት ቆይቷል ብለዋል።
በተለይም በክልሉ የሚገኘውን ውስን መሬት በአግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።
በተለይም በዘንድሮ የበጋ መስኖ ልማት የተለያዩ የአትክልት ዘሮችን፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ሸራ እና የውሃ መሳቢያ ሞተሮችን ለአርሶ አደሮች ማሰራጨት መቻሉን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የብርዕና የአገዳ ሰብሎችን፤ የጥራጥሬ እና የቅባት ሰብሎችን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ረገድም ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።
ግብርናችንን ከዝናብ ጠባቂነት ለማላቀቅም የከርሰ ምድር ውሐ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በዚህም ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ባለፈ አምራቹና ሸማቹን የማገናኘት ስራ በመስራት ኑሮን የማረጋጋት ስራ በትኩረት መሰራቱን ጠቅሰዋል።
በተለይም ህዝቡ በሌማት ትሩፋት እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች እንዲጎለብቱ የመደገፍ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው የዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚነት የማጎልበት ስራም መሰራቱን ገልጸዋል።
በተለይም የወተት፣ ዕንቁላል፣ ስጋ ፣የማር ምርት ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቁመዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በአትክልት፣ በቡና እንዲሁም በእንሰሳት ተዋፅኦ ላይ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግም እየተሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል።
በክልሉ 900 ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ በክልሉ በሚገኙ ሶስት የገጠር ወረዳዎች በተመረጡ 16 ተፋሰሶች ላይ ከ30 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች የተሳተፉበት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የክልሉ መንግስት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማጎልበት የሚያከናውናቸው ሌሎች ተግባራት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
0 Comments