በክልሉ በዘንድሮው የበልግ መህር እርሻ 11 ሺ 956 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን እየተሰራ ነው-አቶ ነስረዲን አህመድ
ሐረር፣ሰኔ 13/2017(ሐክመኮ):-በሐረሪ ክልል በዘንድሮው የበልግ መህር እርሻ 11 ሺ 956 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ነስረዲን አህመድ ገለፁ።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ነስረዲን አህመድ እንደገለፁት በዘንድሮው የበልግ መህር እርሻ 11 ሺ 956 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡
ከዚህ ውስጥም 2 ሺ 400 ሄክታሩ በቶሎ ደራሽ የማሽላ ክላስተር የሚሸፈን መሆኑን አክለዋል።
ከዚህም 355 ሺ 240 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙን ምክትል ቢሮ ሀላፊው ጠቁመዋል።
ይህም ምርታማነትን ይበልጥ በማጎልበት በተለይ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር እየተደረገ የሚገኘውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህንን ለማሳካትም ለአርሶ አደሩና ግብርና ባለሞያዎች ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ የበቆሎና በቶሎ ደራሽ የማሽላ ምርጥ ዘር ቀርቦ በወረዳዎች በኩል ለአርሶ አደሩ እንዲሰራጩ ተደርጓል።
በቀጣይም 12 ሺ 500 ኩንታል ዳፕ እና ዩሪያ ማዳበሪያ በማህበራት በኩል ለማቅረብ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ምክትል ቢሮ ሀላፊው አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ የስንዴ ዘር ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ እየተሰራ እንደሚገኝ ምክትል ቢሮ ሀላፊው አያይዘው ገልፀዋል።
0 Comments