Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ በበጋ መስኖ 4 ሺ 700 ሄክታር አታክልት እና ፍራፍሬ እየለማ ነው

ሀረር 3/2017(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል በበጋ መስኖ 4 ሺ 700 ሄክታር አታክልት እና ፍራፍሬ እየለማ ነው።

በክልሉ በበጋ መስኖ እየለሙ ከሚገኙ አታክልት  እና ፍራፍሬዎች መካከል ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመን፣ ቃርያ፣ፓፓያ ፣ ሙዝ እና ሌሎች የአታክልት እና ፍራፍሬ ዓይነቶች ይገኙበታል።

በበጋ መስኖ ልማት እየለሙ የሚገኙ አታክልት እና ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ከፍተኛ አበርክቶ ይኖራቸዋል።

በበጋ መስኖ ልማቱ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ ግብዓት ከማቅረብ ጀምሮ እየተደረገ  ያለው የባለሙያ ድጋፍም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish