Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ በቅርስ ልማት እና ጥበቃ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

ሐረር፤የካቲት 18/2017(ሐክመኮ):-በሀረሪ ክልል አበረታች የቅርስ ልማት እና ጥበቃ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን ቀድሪ ገለፁ።

የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ 6ተኛ ዙር 4ተኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በስብሰባዉ ላይ ባለፉት 6 ወራት በትምህርት ፤በባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም የሐረሪ ጉባኤ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ከሚገኙ የክልሉ ተወላጆች ጋር ያካሄዳቸው የጋራ ውይይት መድረኮች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ ላይ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት በክልሉ በቅርስ ጥበቃ እና ልማት ዘርፍ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል።

በተለይ በአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የተከናወነው የመልሶ ልማት ስራ ቅርሱን ለጎብኚዎች እና ነዋሪዎች ምቹ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

ይህም በቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃትን በመፍጠር የቱሪዝም ፍሰቱ እንዲጎለብት ማስቻሉን ጠቁመዋል።

የክልሉን ቋንቋ ከማሳደግ አንፃርም የተጀመሩ አበታች ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል የሀረሪ ክልልን በኮሪደር ልማት ፅዱ፤ውብ እና በስርዓት የምትመራ ምቹ ከተማ ለማድረግ እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎች አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ በተከናወኑ ሰፋፊ የልማት ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶች የአመራሩ ና ህዝቡ ጠንካራ የቅንጅት ስራ ውጤቶች መሆነቸውንም አክለዋል።

በቀጣይም ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ በሁሉም ዘርፍ በተከናወኑ የልማት ስራዎች የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገልፀዋል።

በመድረኩ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፤የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ፤የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪምን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የቀረቡ ሪፖርቶች ከቤቱ የተሰጣቸውን ግብዓት አካተው እንዲፀድቁ በማድረግ የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ሲያካሂደው የነበረውን 6ተኛ ዙር 4ተኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባው አጠናቋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish