በክልሉ በሌማት ትሩፋት የተገኙ ውጤቶችን ማስፋት ይገባል የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
በሀረሪ ክልል በሌማት ቱርፋት የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለፁ።
በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ ከፍተኛ አመራሮቾ ልዑካን ቡድን ከሀረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮቾ ጋር በመሆን በክልሉ በግብርና ዘርፍ ፣ የሌማት ትሩፋት እና እየተገነቡ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እየተመለከተ ይገኛል።
በመስክ ምልከታው ላይ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በክልሉ በሌማት ትሩፋት አበረታች ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይ ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ብሎም ከስደት ተመላሽ ወጣቶች በክልሉ መንግስት በተደረገላቸው ድጋፍ በሌማት ትሩፋት ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ውጤታማ መሆን መቻላቸውን በዚህም የአመጋገብ ስርዓቱ መለወጡን ገልፀዋል።
የሌማት ትሩፋቱ የይቻላል መንፈስን በመፍጠር የማህበረሰቡ የስራ ባህልን መቀየሩን በመጠቆም በዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን ማስፋት እንደሚገባም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ታንኳይ ጆክ በበኩላቸው በክልሉ በሌማት ትሩፋት በተሰራው ስራ ለወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ምርቱን በቅዳሜ ገበያ በማቅረብ ገበያውን ማረጋጋት መቻሉን ገልፀዋል።
የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ለሌማት ትሩፋት ልዩ ትኩረት በመስጠት ከስደት ተመላሽ ወጣቶችን በዘርፉ እንዲሰማሩ በማድረግ ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል።
ቢሮው ለአርሶ አደሩ የተለያዩ ግንዛቤዎችን መፎጠሩን ተከትሎም አርሶ አደሩ ከጫት ምርት በተጓዳኝ በማሳው ውስጥ የጓሮ አትክልቶችን እያለማ ተጠቃሚ መሆን መቻሉን ገልፀዋል።
በዚህም ገቢያቸውን ከማሳደግ ባለፈ የምግብ ዋስትናውን ማረጋገጥ መቻሉን አሰገንዝበዋል::






0 Comments