Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ ለ 70 ሺህ ህፃናት የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ይሰጣል-ዶ/ር አብዲ አሚን

በሐረሪ ክልል ለ 70 ሺ ህፃናት የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ለመስጠት በዘመቻ እንደሚሰራ የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አብዲ አሚን አስታወቁ።

በሐረሪ ክልል ከመስከረም 30 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት የልጅነት ልምሻ በሽታ(ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አብዲ አሚን አስታውቀዋል።

መስከረም 30 በሚጀምረው የሦስተኛ ዙር የክትባት ዘመቻ 70 ሺህ ህፃናትን ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉንም አክለዋል።

ክትባቱ ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በህፃናት መዋያና በጤና ተቋማት የሚሰጥ መሆኑም ሀላፊው ጠቁመዋል።

በዘመቻው ከፖሊዮ ክትባት በተጨማሪ መደበኛ የህፃናት ክትባት መውሰድ ጀምረው ያቋረጡ እና መደበኛ ክትባት ላልጀመሩ ህፃናትም መደበኛ ክትባት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን ኃላፊው አስገንዝበዋል።

የልጅነት ልምሻ በሽታ(ፖሊዮ) ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ ከፍተኛ የመከሰት እድል ያለው በሽታ መሆኑን ጠቁመው በሽታውን በክትባት መከላከል እንደሚቻል አንስተዋል።

በመሆኑም ከመስከረም 30 ጀምሮ በሚካሄደው የክትባት ዘመቻ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን በማስከተብ ወላጆች፤ማህበረሰቡ እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በመወጣት ለዘመቻው ስኬት የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

Harari #Health #PolioVaccine

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish