Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል- የሀረር ከተማ ነዋሪዎች

ሀረር ሰኔ 18/2016(ሀክመኮ):-የህዝቡን አንገብጋቢ የመሰረተ ልማት ችግሮች ለመቅረፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ማጠናከር ይገባል ሲሉ የሀረር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

በሀረር ከተማ የማህበረሰቡን የረጅም ግዜ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየተከናወኑ የሚገኙ የመንገድ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፤ የቅርስ ጥበቃን ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የከተማው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

በከተማው እየተገነቡ የሚገኙ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግረኛ መንገዶች የከተማውን ውበት ከመጨመርና ለእግረኞች ምቹ ከማድረግ ባለፈ የትራፊክ አደጋን በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተለይ የሀረር ከተማ የሚዳሰስና የማይዳሰስ የአለም ቅርስን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች እና ሙዚየሞች የሚገኙባት መሆኗን ጠቁመው በከተማው የሚገኙ ቅርሶችን ከመጠበቅና ከመንከባከብ አንፃር እየተከናወኑ የሚገኙ የመልሶ ማልማት ስራዎች ከተማዋ በቱሪስቶች ተመራጭና ለነዋሪዎችም ምቹ እንድትሆን የሚያስችል ነው።

ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለክልሉ ህዝብ የረጅም ግዜ ጥያቄ ምላሽ የሰጠ መሆኑን አክለዋል።

በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የአካባቢውን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ኢኮኖሚውን የሚያነቃቁ መሆናቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ በልማት ስራው ለበርካታ የከተማው ነዋሪዎች የስራ እድል መፈጠሩንም ገልፀዋል።

ከተማዋ ጥንት የስልጣኔ መዓከል መሆኗን በማስታወስ እየተሰሩ ያሉ እድሜዋን የሚመጥኑ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አስተያየታቸውን ሰተዋል።

እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ሊሰራ እንደሚገባ የጠቆሙት ነዋሪዎቹ ከመንግስት ጎን በመሆን አሰፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish