በከተማው በ 20 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካማ ዜጎች ተላለፉ
ሀረር፣ጥቅምት 16/2018(ሀክመኮ):-በሀረር ከተማ ከ 20 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካማ ዜጎች ተላለፉ።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመተባበር በሀረር ከተማ ያስገነባቸው መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚ ተላለፉ።
ተጠቃሚዎቹ ቁልፉን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ከሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ እና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሄለን ደበበ እጅ ተረክበዋል።
በቁልፍ ርክክቡ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ እንደገለፁት ከለውጡ ቡሀላ መንግስት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
የአቅመ ደካማ ዜጎችን ኑሮ ማሻሻልም መንግስት ሰብዓዉ ብልፅግናን ከሚረጋግጥባቸው መንገዶች አንዱ መሆኑን አክለዋል።
በዚህም ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሀረር ከተማ 8 አቅመ ደካማ አባወራና እማ ወራዎችን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።
መሰል የበጎ ፈቃድ ተግባራትም ብልፅግና ፓርቲ ማህበራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ለሚገኙ ተግባራት አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሄለን ደበበ በበኩላቸው በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት በተጀመሩ ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ተግባራት የዜጎችን ህይወት ለማሻሻል እየተሰራ ነው ብለዋል።
ዜጎች ደረጃውን የጠበቀ ህይወት እንዲኖራቸው ትኩረት ተሰጥቶ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል።
የበጎ ፈቃድ ተግባራትን በማጠናከር ዜጎች ክብራቸውን የሚመጥን መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
ማህበረሰቡም ተረጅነትን ለማስቀረት እንደ መንግስት በተጀመሩ ተግባራት ላይ በመሳተፍ እርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህልን ማጎልበት ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ፣የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሄለን ደበበ፣የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሊድ አብዱረህማን፣የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለ ስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኢንጅነር መስፍን ነገዎ፣የሚኒስቴር መስራያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
0 Comments