Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በእኛ በኩል አንድ ጥይት አይተኮስም:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በኤርትራ በኩል ከሰሞኑ ጦርነት ይጀመራል የሚል ነገር ቢኖርም ከእኛ በኩል ግን አንድ ጥይት እንደማይተኮስ ለምክር ቤቱ ለመግለጽ እውዳለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ በንግግር እንጂ በግጭት አታምንም፤ ሌላውም ወገን በዚህ ቢመራ የተሻለ ይሆናል ከዚህ ውጪ ያለው ነገር አይጠቅመንምም” ነው ያሉት።

ፍላጎታችን ያለንን ተካፍለን ከወንድም ሕዝቦች ጋር በጋራ እየለማን መኖር ነው፤ ይሄን አልፎ የሚመጣ ካለ ግን እንከላከላለን፤ ለሱም ዝግጁ ነን ብለዋል።

ባለፉት 7 ዓመታት ኢትዮጵያ ከአንድም ጎረቤት ሀገር ጋር ጦርነት ውስጥ አልገባችም ወደፊትም የእኛ መንገድ ይኸው ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ጎረቤት ሀገራትን በሚመለከት አንዳችን ለሌላችን ኅልውና አስፈላጊ ነን፤ ነገር ግን ሁሉም ግንኙነት አልጋ ባልጋ ሊሆን አይችልም፤ ድንበርን ጨምሮ የማያግባቡን ጉዳዮች ይኖራሉ ብለዋል።

ጥቅማችን የተሳሰረ በመሆኑ አብሮ ለመኖር ሰጥቶ በመቀበል መርሕ መተጋገዝ እንጂ የአንድ ሀገር መታመስ ሌላውን ከማጥፋት የዘለለ ጥቅም የለውም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ጠላቶች ነበሯት፤ አሁንም ጠላቶች አሉ፤ ነገር ግን ከፊታቸው እናንሠራራለን፤ ልማታችንም ይቀጥላል፤ ሲሉም አፅንኦት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓለም በተለያዩ ችግሮች ወዲያ እና ወዲህ በምትናወጥበት ወቅት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ሀገር በጥንቃቄ መጓዝ አለባት ብለዋል።

በተለይም ወዳጆቻችንን መጠበቅ አለብን፤ የማይወዱንን ደሞ ማለዘብ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ዝምብሎ ከሚጮኸው ጋር መጮህ ሳይሆን የዓለም ሁኔታን መከታተል እና ሚዛናዊ ሆኖ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish