Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በተወሰዱ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ ቀንሷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በተወሰዱ የተለያዩ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በማብራሪያቸውም፤ በተወሰዱ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ መቀነሱን ተናግረዋል።

ለዚህም በምክንያያትነት የሚጠቀሱት ከአቅርቦት አንጻር በግርብርና ዘርፍ በስፋት መሠራቱ፣ የገበያ ትስስርም ቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን በማስፋት ሻጭና ሸማችን በቀጥታ ማገናኘት በመቻሉ እንዲሁም ድጎማ በመደረጉ ነው ብለዋል።

ከድጎማ ጋር በተያያዘም፤ ባለፈው ዓመት ለሴፍቲኔት 60 ቢሊየን ብር፣ ለማዳበሪያ 84 ቢሊየን ብር፣ ለነዳጅ 140 ቢሊየን ብር ድጎማ መደረጉን ገልጸው፤ ዘንድሮ ለደመወዝ 160 ቢሊየን ብር ጨምረናል ብለዋል።

በአጠቃላ 440 ቢሊየን ብር ገዳማ ለድጎማ አውጥተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የማዕድ ማጋራት ባህል ማደግ፣ የተማሪዎች ምገባ መስፋፋትና የገንዘብ ፖሊሲያችን የኑሮ ውድነትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና አበርክተዋል ብለዋል።

አሁን ያለንበት የጥቅምት ወር የዋጋ ንረትም 11 ነጥብ 7 በመቶ ወርዷል ነው ያሉት።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish