Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ኩንታል ምርት ተገኝቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

በበጀት ዓመቱ በግብርናው ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ኩንታል ምርት ተገኝቷል አሉ የአፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ÷ መንግስት ዘርፉን ለማዘመን ባከናወናቸው ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶችን መመዝገባቸውን አንስተዋል፡፡

በዚሁም የመስኖ ልማትን ለማጠናከር በበጀት ዓመቱ ከስድስት በላይ ከፍተኛ ግድቦች እንዲሁም ከ145 ኪሎ ሜትር በላይ ካናሎች ተገንብተው ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የበጋ መስኖ ልማትን የሚያግዙ ከ100 በላይ አነስተኛ እና መካከለኛ ግድቦች በተለያዩ ክልሎች እየተገነቡ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በግብርና ሜካናይዜሽን በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ትራክተሮች፣ ኮምባይኖሮች እና ሌሎች የግብርና መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደተቻለም ጠቁመዋል፡፡

በዚህም በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ገልጸው÷ ባለፈው ዓመት ከነበረው ምርት ጋር ሲነፃፀር በ300 ሚሊየን ኩንታል ብልጫ እንዳለው አመላክተዋል፡፡

ለበጋ ስንዴ ምርት በተሰጠው ትኩረት እንዲሁም የሌማት ትሩፋት ሥራዎች በዶሮ፣ እንቁላል፣ ማር፣ አሳ እና ወተት ምርቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱንም ተናግረዋል፡፡

ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋልታ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ቢዚህ ዓመትም በዘርፉ 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ለማምጣት መታቀዱን አብራርተዋል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish