በበጀት ዓመቱ ለ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የ2017 በጀት ዓመት ለ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የስራ እድል ፈጠራ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ትልቅ እመርታ ከታየባቸው መስኮች መካከል አንዱ መሆኑን አመልክተዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ ለ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩንና ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮኑ (39 በመቶ ድርሻ) በግብርናው ዘርፍ የተገኘ የስራ እድል መሆኑን ጠቁመዋል።
በአገልግሎት ዘርፍ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን እና በኢንዱስትሪ 680 ሺህ ገደማ ዜጎች ስራ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት በመላክ ስራ እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል።
ከ60 ሺህ በላይ ዜጎች በርቀት ስራ (remote work) የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩት።
የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት እና የርቀት ስራ ላይ የጀመራቸው ስራዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
0 Comments