Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በቀጣዩ በጀት ዓመት የህዝብን ጥያቄ ለሚመልሱ የልማት ስራዎች ትኩረት ተሰቶ ይሰራል-የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት

ሐረር፣ግንቦት 14/2017(ሐክመኮ):-በቀጣዩ የ2018 በጀት ዓመት የህዝብን ጥያቄ ለሚመልሱ የልማት ስራዎች ትኩረት ተሰቶ እንደሚሰራ የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት አስታወቀ።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀጣዩ የ2018 በጀት ዓመት ሊከናወኑ በታሰቡ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱም በቀጣዩ በጀት ዓመት ለህዝብ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ የልማት ስራዎችን በተለይ የመሶብ ፕሮጀክትን ዕውን ለማድረግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ነው የተመላከተው።

በተለይ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች፣የገጠር መንገድ ግንባታ፣ውሃና የመሳሰሉት ፕርጀክቶች ልዩ ትኩረት እንደሚያገኙ ነው የተመላከተው።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish