Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም በጋራ መስራት ያስፈልጋል- ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር 

ሐረር፣ሰኔ 10/2017(ሐክመኮ):-በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቀረት በጋራ መስራት እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ገለጹ።

የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሐረሪ ክልል ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ሴቶችና ህጻናትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ማስቆም ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በማስቀረት ረገድ በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ከለውጡ ወዲህ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጾታዊና አካላዊ ጥቃቶችን በመከላከል ረገድ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን  ጠቁመዋል።

በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃትና ጫናዎችን መከላከል የሁሉም የጋራ ሃላፊነት ሊሆን ይገባል።

በተለይም የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከልና ጥቃቶች ሲከሰቱ የህግ ጥበቃና ከለላ በማድረግ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ሂክማ ኬይረዲን በበኩላቸው እንደ ሀገር በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በመከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮሩ ንቅናቄ መድረኮች በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እያካሄዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል። 

በዚህም ሴቶችና ህጻናትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችንና የህጻናት የጉልበት ብዝበዛ ለመከላከል የሚያስችሉ ህዝባዊ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

ሆኖም ተጨማሪ ስራዎችን በመስራትና ያሉ ውስንነቶችን በማሻሻል ለጥቃት መንስኤ የሆኑ አመለካከቶችን በመቀየር መብትና ደህንነታቸውን ማስጠበቅ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመድረኩ ላይ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ሂክማ ኬይረዲንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish