በራስ አቅም ፈጠራና ወጪ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለሌሎችም አካባቢዎች ምሳሌ የሚሆን ነው- የአዲስ አበባ መስተዳድር የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች
ሐረር፣ሰኔ/12/2017(ሐክመኮ):- በሀረር ከተማ በራስ አቅም፣ ፈጠራና ወጪ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለሎችም አካባቢዎች ምሳሌ የሚሆን መሆኑን የአዲስ አበባ መስተዳድር የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ገለፁ።
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በሐረር ከተማ የሚገኙ የኮሪደር ልማትና የቱሪዝም መዳረሻዎች ተመልክተዋል።
በምልከታው የሐረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የክልሉ መንግስት ለኮሪደር ልማትና ልዩ ትኩረት በመስጠት በራስ አቅም፣ ፈጠራና ወጪ ማህበረሰቡን በማስተባበር የከተማዋን ገጽታ የሚቀይሩ ኘሮጀክቶች መሰራታቸውን ተመልክተናል ብለዋል።
በመስክ ምልከታው ላይ የተገኙ ጎብኚዎች እንደተናገሩት ማህበረሰቡን በማስተባበር የተሰሩ የኮሪደር ልማቶች የሀረር ከተማን ገናናነት የሚመልሱ ናቸው።
በተለይም በጀጎል አለም አቀፍ መልሶ ልማት ስራ የቅርሱን ይዘት በጠበቀ መልኩ የተከናወነው ስራም ለሌሎች ጥንታዊና የቅርስ ከተሞች በተሞክሮነት የሚወሰድ ስለመሆኑ አንስተዋል።
በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና ዙሪያ የኮሪደር ልማት ስራዎችም አካባቢውን ፅዱ፣ ውብና ማራኪ ተደርጎ መሰራቱ የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስብ ቦታ እንዲሆነ ማስቻሉንም አክለዋል።
ይህም ሐረር ያላትን የታሪክ፣ ባህልና ቅርስ እምቅ አቅሞችን ጠብቆ በማልማትና በመንከባከብ የጀጎል ቅርስ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹ ማድረግ መቻሉን በመመልከታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
በክልሉ በራስ አቅም፣ ፈጠራና ወጪ የተከናወኑ ስራዎች ለሎችም አካባቢዎች ምሳሌ የሚሆን ነው ያሉት አመራሮቹና በኮሪደር ልማት ለዜጎች የስራ እድል ፈጠራ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ነው ያነሱት።
ስራዎቹም ከተማዋን ምቹና ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን ትልቅ አስተዋጽኦ ከማበርከቱንም ባሻገር ከተማዋ ለኑሮ ምቹ እንድትሆን የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
#AbadirPlaza #Harari #corridordevelopment #News #ዜና #HararJugol #UNESCOWorldHeritagesite #UNESCOCitiesforPeacePrize #Thelivingmuseum
#World_TourismCitiesFederation #OrganizationofWorldHeritageCities
#Shuwalidfestival #Visitharar #VisitEthiopia
0 Comments