Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በማህበራዊ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል -አቶ ኦርዲን በድሪ

በክልሉ በማህበራዊ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ቀጥሎ ባካሄደው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ግምገማ በማህበራዊ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በግምገማው ወቅት እንደገለፁት ባለፉት 3 ወራት በማህበራዊ ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በማህበራዊ ዘርፍ የሰዎችን ህይወት መሻሻል መሰረት ያደረጉ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም አክለዋል።

በተለይ የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለው ስራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን በመጠቆም የተመዘገበውን ውጤት ለማሻሻል ልዩ ትኩረት ሰቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በተለይ ክህሎት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋን በመፍጠር ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በመሆኑም የትምህርት ጥራትን እና የተማሪ ውጤትን ከማሻሻሉ ስራ በተጨማሪ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ የክትትል ስራ መስራት ይገባል ብለዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳለጥ ብቃት ያለው የሰው ሀይል እና ግብዓቶችን በማሟላት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የዜጎችን ምርታማነት በማሳደግ ማህበራዊ ቀውሶችን ለመቀነስ የሚያስችል እስትራቴጂ በመንደፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁት።

በተለይ ሀረር ያላትን የአብሮነት፣ መቻቻል እና የሰላም የዳበሩ ማህበራዊ እሴቶች በአግባቡ በመጠቀም በማህበረሰቡ መካከል የወንድማማችነት መንፈስን መፍር እንደሚገባ ነው የጠቆሙት።

በሌላ በኩል በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አመላክተዋል።

በተለይ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ የተሰራው ስራ የውጭ እና አገር ውስጥ ጎብኚዎች ፍሰት እንዲጨምር ማስቻሉን ገልፀዋል።

በቀጣይም ክልሉ ያሉትን የቱሪዝም መዳረሻዎች በአግባቡ አልምቶ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish