Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሐረሪ ክልል”የመሐሉ ዘመን”በሚል መሪ ቃል በቀረበ ሰነድ ላይ ውይይት መካሄድ ጀመረ 

ሐረር፤ሚያዝያ 27/2017(ሐክመኮ):-በሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት”የመሐሉ ዘመን”በሚል መሪ ቃል ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በቀረበ ሰነድ ላይ ውይይት ማካሄድ ጀመረ። 

ውይይቱን ያስጀመሩት በሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንደገለፁት ውይይቱ እንደ አገር የተጀመረው ለውጥ፤ስኬትና ተግዳሮት ላይ ውይይት የሚደረግበት ነው። 

በተለይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመሻገር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ውይይት በማድረግ ለቀጣይ ጉዞ እና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ላስቀመጠው አቅጣጫ ተፈፀሚነት ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑ ገልፀዋል። 

ውይይቱ በቀጣይ በተቋማት እንዲሁም በየደረጃው ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ጌቱ ወዬሳ ጠቁመዋል። 

በመርሀ-ግብሩ ላይ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ አባል ወ/ሮ አሚና አብዱልከሪም፣ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፤የሐረሪ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish