Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀገራዊ ምክክር የሴቶች፣ የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች የነቃ ተሳትፎ ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባል – ኮሚሽኑ

በሀገራዊ ምክክር የሴቶች፣ የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች የነቃ ተሳትፎ ተጠናከሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

“የሴቶች፣ የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች ሚና እና አስተዋጽኦ ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ የውይይት መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ በመድረኩ እንደገለጹት፤ እንደሀገር የሚስተዋሉ አለመግባባቶችን በምክክር በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው።

የምክክር ኮሚሽኑ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በአጀንዳ ልየታ፣ በምክክሩ ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን የመለየትና ሌሎች ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የአጀንዳ ሃሳቦችን ባሰባሰበበትና በሀገራዊ ምክክሩ ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን በለየባቸው መድረኮች ወጣቶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን ማሳተፉን ተናግረዋል።

በየመድረኩም የሴቶች፣ የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎና እገዛ ከፍተኛ እንደነበር ኮሚሽነር ሙሉጌታ አመልክተዋል።

በተለያዩ አደረጃጀቶች የታቀፉ የማህበረሰብ ክፍሎች ሀገራዊ መግባባት ሊፈጠርባቸው ይገባል ያሏቸውን የአጀንዳ ሃሳቦች በማደራጀት ለኮሚሽኑ ማስረከባቸውን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ስለኮሚሽኑና ስለምክክር ሂደቱ ሕዝቡ ግንዛቤ እንዲጨብጥ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ማበርከታቸውን ጠቅሰው ይህ ትብብርና እገዛ ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚዘልቀው የውይይት መድረክ ከሐረሪ ክልል እና ከድሬዳዋ አስተዳደር የተውጣጡ ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ተሳታፊ መሆናቸው ተመላክቷል።

መድረኩ በሀገራዊ የምክክር ሂደት ላይ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞችን አበርክቶ ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish