Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረር ከተማ 1 ለ ሺ 548 መንገዶች አዲስ እና ዘመናዊ የአድራሻ መለያ ቁጥር ለመስጠት እየተሰራ ነው -የሐረር ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

በሀረር ከተማ 1 ለ ሺ 548 መንገዶች አዲስ እና ዘመናዊ የአድራሻ መለያ ቁጥር ለመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ የሐረር ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የአድራሻ መለያ ቁጥር እየተሰጣቸው የሚገኙት 1 ሺ 548 መንገዶች ቀደም ሲል ስያሜ ያልተሰጣቸው መሆናቸው ተመላክቷል።

መንገዶቹ በአዲስ ዲጂታል የአድራሻ ሥርዓት መሰረት ስያሜና መለያ ቁጥር እንደሚያገኙ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከመንገዶቹ ጋር ትስስር ያላቸው 10 ሺህ ቤቶች አዲስ የቤት ቁጥር እንደሚሰጣቸዉ ገልጸዋል።

ስራው ከተጀመረበት ግዜ ጀምሮ ከ 600 በላይ ቤቶች ላይ የቤት ቁጥር የመለጠፍ እና በ 110 መንገዶች ላይ (አቅጣጫ ጠቋሚ) ታፔላ መሰቀሉም ተጠቁሟል።

በከተማው 17 ጎዳናዎች ፤ 62 መንገዶች ፥ 20 ንኡስ መንገዶች፥ 850 የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፥489 ዘላቂ ያልሆኑ/ውስን / መንገዶችና 110 የግለሰብ መንገዶች ባጠቃላይ 1 ሺ 548 መንገዶች በኮድ(ቁጥር) ተሰይመዋል።

1 ሺ 29 ታዋቂ ቦታዎች መረጃዎች (ኢንሹራንሶች፥ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፥ ሆቴሎች ፥ ሆስፒታሎች ፋርማሲዎች ፥የቱሪስት መዳረሻና ታሪካዊ ስፍራዎች ፥ የሀይማኖት ተቋማት፣የመንግስት ተቋማት ፥ ፖሊስ ጣቢያዎችና የፀጥታ ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች መረጃዎች ተሰብስበው ወደ ሲስተም መግባታቸው ተመላክቷል።

የሀረር ከተማ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የዲጂታል አድራሻ ስርአት እንዲኖራት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ከኢትዮጵያ ጂኦስፓሺያል እና ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ጋር በ2016 ግንቦት ወር ላይ የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም በ2017 በጀት አመት በመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ስር የዲጂታል አድርሻ ስርአት ትግበራ አስተባባሪ ቡድን ተደራጅቶ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል።

የዲጂታል የአድራሻ ሥርዓቱ የቦታዎችን አቅጣጫ፣ ርቀትና የትራፊክ እንቅስቃሴን የሚጠቁሙና በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳዎች ያሉት ሲሆን በተለይ የሀረር ከተማ የቱሪስት መዳረሻ እንደመሆኗ መጠን ማንኛውንም ስፍራ በቀላሉ
ለማግኘት የሚያሰችል ነው።

የዲጂታል አድራሻ ስርአት ፕሮጀክት አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሀገር አቀፍ እንዲሁም በክልልና ከተማ ደረጃ ምቹ እና ዘመናዊ ከተሜነት እና የዘመናዊ ማህበረሰብን /smart city and smart society/ ለመገንባት እየተደረገ ያለውን ጥረት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተለይ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሽል የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያቀል ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል።

የዲጅታል አድራሻ ስርዐቱን ተግባራዊ ለማድረግ በጂኦስፓሺያል እና ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት የለማ መተግበርያ (አኘሊኬሽን) በአሁኑ ወቅት ስራው ተጠናቅቆ በሙከራ ላይ የሚገኝ ሲሆን መተግበሪያው በአራት ቋንቋዎች የሚሰራ ነው።

በዚህም መሰረት መተግበሪያውን የሐረሪ፤ኦሮሚፋ፤ አማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋን በመጠቀም አድራሻዎችን ለመፈለግ ያስችላል።

የዲጂታል አድራሻ ስርዐቱ የመሬት ላይ መቆጣጠሪያ ነጥቦችን፥የመንገድ ላይ ካሜራዎችን ሲሲቲቪ/ ካሜራ/ ና ሶስቱን የገጠር ወረዳዎች የሚያገናኙ ዋናዋና መንገዶች እና የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ሲስተሙ እንዲገቡ መደረጉ ሲስተሙን ከሌሎች ከተሞች ልዩ እንደሚያደርገውም ተጠቁሟል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish