Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረር ከተማ የኮሪደር መልሶ ማልማት ስራ ልዩ ትኩረት ተሰቶ ወደ ስራ ተገብቷል -አቶ ሙክታር ሳሊህ

በሀረር ከተማ የኮሪደር መልሶ ማልማት ስራ ለማከናወን ልዩ ትኩረት ተሰቶ ወደ ስራ መገባቱን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር መዓረግ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ ገለፁ።

በሀረር ከተማ ከሀማሬሳ እስከ አራተኛ ድረስ የተለዩ አካባቢዎችን ከማህበረሰቡ ጋር በትብብር መልሶ ማልማት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር መዓረግ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ የኮሪደር መልሶ ልማት ስራውን ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በጥራትና ፍጥነት ለማከናወን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በክልሉ ካሁንቀደም በተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተማውን ገፀታ መቀየር መቻሉን የጠቆሙት አቶ ሙክታር በጅምር ስራው የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስፋት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በተለይ ክልሉን ለኑሮ እና ስራ ምቹ ለማድረግ በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች የኮሪደር ልማት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ ሙክታር ሳሊህ አካባቢውን ከመንገድ ጋር አስተሳስሮ ለማልማት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የኮሪደር ልማት እና መልሶ ልማት ስራው የአካባቢን ገፅታ ከመቀየር ባሻገር ምቹ የመኖሪያ አካባቢን በመፍጠር የቱሪዝም ፍሰቱን የሚያሳደግ እና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።

በመልሶ ልማት ስራው ለአካባቢው ነዋሪዎች ቅድሚያ በመስጠት በግል ብሎም በማህበር ተደራጅተው የሚያለሙበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ገልፀዋል።

ስራውን በአጭር ግዜ ጀምሮ ለማጠናቀቅ የአካባቢውን ነዋሪዎች ያሳተፈ ኮሚቴ ተዋቅሮ የመልሶ ልማት ስራውን ለማስጀመር እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው የኮሪደር እና መልሶ ልማት ስራው ለኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ ልማቱን እንደሚደግፉ ገልፀዋል።

የመልሶ ልማቱ ለአካባቢው ነዋሪዎች የረጅም ግዜ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ መሆኑም ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish