Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል 4 ማደያዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል-የሀረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ

በሀረሪ ክልል 4 ነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ ገለፁ።

በሀረሪ ክልል ህገ -ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ ገለፁ።

ኤጀንሲው ባከናወነው የቁጥጥር ስራም ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት የፈፀሙ 4 ማደያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት 2 ማደያዎች እስከ ሁለት ወር በሚደረስ እገዳ የተቀጡ ሲሆን ሁለቱ በብር መቀጮ መቀጣታቸውን ነው ያስታወቀው።

ማደያዎቹ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ እንዲፈፀም የተቀመጠውን መመሪያ በመተላለፍ በካሽ ሲሸጡ የነበሩና ከነዳጅ መሸጫ ታሪፍ ጭማሪ በማስከፈል በህገ-ወጥ መንገድ ሲገበያዩ የነበሩ መሆናቸውንም አክለዋል።

እርምጃ የተወሰደባቸው ማደያዎቹ 3 በከተማ እና አንድ በገጠር ወረዳ የሚገኙ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ኤጀንሲው ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ላይ የጀመረውን ቁጥጥር በማጠናከር ህገ-ወጥ ግብይት የሚፈፅሙ ማደያዎችን ተጠያቂ የማድረጉን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ሸሪፍ ሙሜ ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish