በሀረሪ ክልል ግምታዊ ዋጋው ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የኮንትሮባንድ እቃ ተያዘ
በሀረሪ ክልል ግምታዊ ዋጋው ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ጣሰው ቻለው እንደገለፁት የኮንትሮባንድ እቃው የተያዘው ፖሊስ ባደረገው የተጠናከረ ክትትል ነው።
የኮንትሮባንድ እቃው የተያዘው በኮድ 3 ታርጋ ቁጥር 06153 ድሬ በሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ መሆኑን ጠቁመው እቃው ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድተዋል።
የተያዘው የኮንትሮባንድ እቃ በዋናነት ሲጋራና ሌሎች ቁሳቁሶችን ያካተተ ነውዐብለዋል።
ህብረተሰቡ እና ፖሊስ ያደረጉት ቅንጅት ለኮንትሮባንድ ዕቃው መያዝ ትልድ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው፤ ህብረተሰቡ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።


0 Comments