በሀረሪ ክልል የ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ የመንግስት ሴክተር ተቋማት እና ወረዳ መስተዳድሮች የዕቅድ አፈፃፀም ምዝና መርሃግብር ከዛሬ ጀምሮ መካሄድ መጀመሩን የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ገለጸ።
የሀረሪ ክልል ፕላን ኮሚሽን በክልሉ በሚገኙ በሁሉም የመንግሥት ተቋማት እና ወረዳዎች ከዛሬ ሰኔ 25/2017 ጀምሮ በአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት የአፈጻጸም ምዘና መካሄድ መጀመሩን አስታውቋል።
የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢብሳ ኢብራሂም በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ ዘጠኝ ቀናት በክልሉ በሚገኙ የመንግስት ተቋማትና ወረዳዎች የሚካሄደው የአፈጻጸም ምዘና ውጤትን መሰረት ያደረገ ፣ ግልጽ ፣ ወጥና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማስፈጸም ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
መደበኛ የልማት ዕቅድ አፈጻጸም ምዘናው መርህ ተቋማት በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት ሥርዓት አስቀድመው ያስገቡት ሪፖርትን ግልጽና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ የክትትልና ግምገማ ስርዓት በተከተለ አግባብ በተጨባጭ ስራው መሬት ላይ መኖሩ በአካል በሰነድ በተግባር የሚረጋገጥበት ነው ብለዋል።
አያይዘውም በመርሃግብሩ ከፕላን ኮሚሽን ጋር የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት፣ የካቢኔ ጉዳዮች ፅ/ቤት እና የክቡር ፕሬዝዳንቱ አማካሪዎች ቡድን በጋራ የሚሳተፉበት በመሆኑ በተቋማትና ወረዳዎች የሚካሄደው የአፈጻጸም ምዘና በክልሉ የተናበበ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ሥርዓትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል።
በየትኛውም የመንግስት ተቋም የሚቀርቡ ሪፖርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እና ትክክለኛ መሆናቸው እንደሚረጋገጥ ጠቁመዋል።
የአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር፤ የምዘና ስርዓቱ ሂደት፤የዘርፎች ስትራቴጂክ ግቦች፣ ዋና ዋና ተግባራት እና ዝርዝር ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች ልየታ፤ ለዉጤታማ ምዘና ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሚካሄደው ምዘና ተቋማት ያላቸው አፈፃፀም እየተገመገመ በአፈፃፀማቸው መሰረት ውጤት የሚሰጥና ደረጃዎች የሚቀመጥበት ይሆናል ብለዋል።
የተቋማት ምዘና ግልጽና ፍትሃዊ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
#Harari #plancommission #News #ዜና
0 Comments