በሀረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ስራዎች ማጠናከር ይገባል፦ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
በሀረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ስራዎች ማጠናከር ይገባል ሲሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ገለፁ።
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ የሚኒስትር መ/ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን ማምሻውን በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እንክብካቤና ልማት ስራዎች እና በመደመር ትውልድ መጽሀፍ የተገነባው የሀረር ኢኮ ፓርክን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት ሀረር ከተማን ተመራጭና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተመልክተናል።
በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቁመዋል
በተለይም ከ”መደመር ትውልድ” መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘው ገቢና የክልሉ መንግስት ባደረገው ድጋፍ የተገነባው የሀረር ኢኮ ፓርክ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት መገንባቱ ለሌሎች ፕሮጀክቶች ተሞክሮም የሚወሰደበት መሆኑንም አመልክተዋል።
የክልሉን የቱሪስት መስህብና የጎብኚዎችን ፍሰት በሚያጠናክር መልኩ ማልማት በሚያችል ሁኔታ ፓርኩ መገንባቱን ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ኢኮ ፓርክ የክልሉን ባህል፣ ታሪክና ቅርስ በተገቢው ሁኔታ የሚያሳይና ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ የሚያስተላልፍ መሆኑን ተናግረዋል።
በጁገል የውስጥ ለውጥ መንገድ ስራ በአካባቢው ያለውን ስነ ምህዳር በጠበቀ መልኩ የተሰሩ ስራዎች ሳቢና ማራኪ ናቸው ብለዋል።
በጉብኝቱ ላይ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ፣የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የሚኒስትር መ/ቤቱ አመራሮች ተገኝተዋል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒና የሚኒስቴር መ/ቤቱ የሥራ ኃላፊዎቹ ነገ በክልሉ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።




0 Comments