በሀረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ስራዎች ማስቀጠል ይገባል፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ም/ፕሬዝዳንት::
በሀረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ስራዎች ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ኃይለእየሱስ በቀለ ገለፁ።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ኃይለእየሱስ በቀለ የተመራ የንግድ ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እንክብካቤና ልማት ስራዎችና በውስጡ የሚገኙ ጥንታዊ፣ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ የመስህብ ስፍራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ኃይለእየሱስ በቀለ እንዳሉት ሀረር ከተማን ተመራጭና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተመልክተናል።
በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቁመው
በተለይም በጁገል የውስጥ ለውጥ መንገድ ስራ በአካባቢው ያለውን ስነ ምህዳር በመጠቀም ባህልና እሴትን በጠበቀ መልኩ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ሳቢና ማራኪ ናቸው ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የልዑካን ቡድኑ የሀረሪ ባህል ሙዝየምን፣ አብደላ ሸሪፍ የግል ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎች ታሪካዊ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ኃይለእየሱስ በቀለ የተመራው የንግድ ባንክ እና የጤና ሚኒስትር የመሠረተ ልማት ዳይሬቶሬት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን በክልሉ ከዚህ ቀደም በባንኩ የበጀት ድጋፍ የተገነባው የሸንኮር ጤና ጣቢያ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ባንኩ ጤና ጣቢያውን ለማጠናከር እና ለማስፋት በቀጣይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ከክልሉ ጤና ቢሮ መግባባት ተደርሳል።
በጉብኝቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ኃይለእየሱስ በቀለ የተመራው የንግድ ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን ፣የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂን ጨምሮ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።




0 Comments