Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል ከ13ሺህ ሊትር በላይ በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

ሀረር ጥር 12/2017(ሀክመኮ):- በሀረሪ ክልል በአንድ ወር ግዜ ውስጥ 13 ሺህ 480 ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንዳሉት በክልሉ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለማስቆም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በተሰራው ስራ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 13ሺ 480 ሊትር ነዳጅ ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ነዳጁ በቁጥጥር ስር የዋለው በኬላዎች ላይ በተደረገ ፍተሻ እንዲሁም ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በሕገ ወጥ መንገድ በቤት ውስጥ ተከማችቶ የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

ነዳጅን በበርሜል በህገ ወጥ መንገድ ሲያሸሹ የተደረሰባቸው እና በመኖሪያ ቤታቸው ደብቀው የተገኙ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

መንግስት ከፍተኛ በጀት መድቦ የሚያስገባው ነዳጅ ለታለመለት አላማ ሊውል ይገባል ያሉት ኮሚሽነሩ በህገወጥ የነዳጅ ግብይት በሚሳተፉ አካላት ላይ በቀጣይም የተጠናከረ ክትትል በማድረግ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

በቀጣይም ሕገ ወጥ ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉም ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን ጠቁመዋል።

ማህበረሰብ በአካባቢው ሕገ ወጥ የነዳጅ ግብይትን ሲመለከት በአካባቢው ለሚገኙ የፖሊስ ጽ/ቤት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አስተላልፈዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish