Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል ባለፍት ስድስት ወራት በጤናው ዘርፍ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ 

በሀረሪ ክልል ባለፍት ስድስት ወራት የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳደግ በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ  አስታውቋል።

የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ በጤናው ዘርፍ ባለፍት ስድስት ወራት የተከናወኑ አበይት ተግባራት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

የቢሮው ሃላፊው በመግለጫቸው እንደተናገሩት በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

ባለፍት ስድስት ወራት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የጤና ተቋማት 462, 913 ዜጎች በተመላላሽ ህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልፀዋል። 

የቢሮ ሃላፊው በመግለጫቸው እንደተናገሩት በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን እና የጤና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው ብለዋል። 

ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና በማከም ረገድም የተሰሩ ስራዎችም አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የገለፁት አቶ ያሲን ለዚህም ባለፉት ስድስት ወራት በወባ በሽታ ምክንያት አንድም ሞት አለመመዝገቡ ለተመዘገበው ውጤት በማሳያነት ጠቅሰዋል። 

ለእናቶችና ህፃናት ጤና  እንዲሁም ለማህፀን በር ካንሰር፣ ለስኳርና ለደም ግፊት የቅድመ ምርመራና ህክምና ስራዎች ትኩረት በመስጠት መሰራት መቻሉን ጠቁመዋል። 

ባለፉት ስድስት ወራት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታይ የባህሪና የአሠራር ተግዳራቶችን በመፍታት የመልካም አገልግሎትን በጤናው ዘርፍ ለማረጋገጥ ውጤታማ ስራዎች ተስርተዋል ያሉት ሀላፊው የህክምና ግብአትና መድሀኒት አቅርቦት ችግሮችን ለመቋቋም የተለያዩ ስልቶች ተተግብረው ተግዳሮቱን ለመፍታት ተሰርቷል ብለዋል።

የክልሉን ነዋሪ የተሟላ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ከማስቻል ባለፈም ሀረር ከተማን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑና የግሉ የጤና ዘርፍም በዚህ ረገድ ሚናውን እንዲወጣ ተገቢ አመራር እየተሰጠ እንደሆነ ጠቁመዋል። 

ከዚህ ባሻገር የጤና መሰረተ ልማት በማስፋፋት ረገድም ልዩ ትኩረት በመስጠት ሁለት ፕሮጀክቶች የተጠናቀቁ መሆኑን ገልጸዋል። 

በቀሪው የበጀት ዓመትም የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር እየጨመረ የሚገኘው የህብረተሰቡን የጤና ፍላጎት ለማርካት የሚያስችል ስራ ይሰራል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish