Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል ባለፈው ስድስት ወራት ከ 2 ቢሊዬን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 41 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን የክልሉ የኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ገለፀ። 

የሀረሪ ክልል የኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ እስማኤል ዩሱፍ የተቋሙ የስድስት ወራት አፈጻጸም በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል። 

በመግለጫቸውም ባለፍት ስድስት ወራት በበጀት አመቱ ለዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል ለመፍጠር ከታቀደው 5,034 የስራ እድል ውስጥ ለ 4,822 ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ተናግረው አፈጻጸሙም 95 በመቶ መሆኑን ገልፀዋል። 

ከዚህም ውስጥ በከተማ ለሚገኙ 2,556 የስራ ዕድል እንዲሁም 1,842 በገጠር ወረዳ ለሚገኙ ወጣቶች ስሆን 424 የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት የተፈጠረላቸው ዜጎች መሆኑን አስረድተዋል። 

የስራ ዘርፎቹም በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች መሆኑንም ነው የገለፁት። 

ባለፍት ስድስት ወራት ለኢንተርፕራይዞች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት መሰጠቱን ገልጸዋል። 

በመንግሥትና በግል ተቋማት መካከል ውጤታማ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ባዛር መዘጋጀቱን አክለው ገልጸዋል። 

በስድስት ወራት ግዜ ውስጥ ለኢንተርፕራይዞች የማምረቻና የመሸጫ ስፍራዎችን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር 25 ሼዶችን ለኢንተርፕራይዞች መሰጠቱን ጠቁመዋል።

በክልሉ ከ 2 ቢሊዬን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 41 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል። 

የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሽፋንን ለማሳደግ 1,611 ለሚሆኑ ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን (online) የተደገፈ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ገልጸው ከንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከ 2 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብን ገልጸዋል። 

የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የሚያስችሉ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ የማጠናከር ስራዎችን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። 

የሕዝቡን ችግር በማባባስ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚሯሯጡ ነጋዴዎች ላይ አስተማሪ የሆነ ህጋዊ ዕርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ጠቁመዋል። 

የህዝባችን የኑሮ ውድነት ለማቃለል በተለይም መሰረታዊ የሆኑ ፍጆታዎችን የማቅረብ ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል። 

ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የጥሬና  የፋብሪካ ውጤቶች የግብዓት አቅርቦትን ለማሻሻል በ 6 ወር 287 ቶን በላይ ግብዓት ለማቀረብ ተችሏል፡፡

ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሊዝ ፋይናንስ አቅርቦትን በብር 12,879,864 ለማሳደግ ታቅዶ ብር 30,300,000 የቀረበ ሲሆን አፈጻጸሙ 100% ነው ብለዋል።

በቀጣይ ሰፋፊ የስራ እድልን ለመፍጠርና የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት ስራ በከፍተኛ  ትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish