በሀረሪ ክልል መሬት ወስደው ለአመታት ሳያለሙ በቆዩ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ ይወሰዳል- አቶ ኦርዲን በድሪ
የክልሉ የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት በምደባ ወስደው ለአመታት ሳያለሙ በቆዩ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወሰድ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ እንደተናገሩት በክልሉ በመንንግስት እና በግል ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
“”በአብዛኛው ፕሮጀክቶች አፈፃፀም መሻሻል የታየባቸው ቢሆኑም አንዳንድ የመንግስት እና የግል ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አዝጋሚ እንደሆኑ ተመልክተናል”
በቀጣይ በመንግስት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ ርብርብ እንደሚደረግ ጠቁመው በግል ኢንቨስትመንቱ ዘርፍ የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት በምደባ ወስደው ለአመታት ሳያለሙ በቆዩ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ብለዋል።



0 Comments