Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል ለሚገኙ ለብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የምሳ ግብዣ መርሀ-ግብር ተካሄደ

ሐረር፤ሚያዝያ 12/2018(ሐክመኮ):-በሀረሪ ክልል ለሚገኙ ለብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የምሳ ግብዣ መርሀ-ግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት ተካሄደ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት የብሄራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ በመሳተፍ እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። 

የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ወጣቶች እየሰጡት ያለው አገልግሎት የማህበረሰቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በማቃለል አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡበት እንደሚገኝም ገልፀዋል። 

በተለይ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ መርሀ-ግብሩ ቀድሞ የነበረውን እርስ በእርስ የመረዳዳት እሴቶ በማጎልበት አበርክቶው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል። 

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በዓሉን በወንድማማችነት መንፈስ እርስ በዕርስ በመደጋገፍ ማሳለፍ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል። 

በመርሀ -ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና የብሔራዊ በጎ ፈቃድ መርሀ-ግብር ተሳታፊ ወጣቶች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish