ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የሁለተኛ ዙር የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስጀምረዋል
ሐረር፣ሰኔ 26/2017(ሐክመኮ):-የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ሁለተኛውን ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ብሔራዊ ፈተና አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ፈተናውን በሐረር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ያስጀመሩ ሲሆን በተለያዩ የፈተና ማዕከላትም በመገኘት የፈተና ሂደቱን ተመልክተዋል።
በወቅቱም ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን እንዲፈተኑ አበረታተዋል።
በሁለት ዙሮች እየተሰጠ በሚገኘው በዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12 ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በክልሉ 2 ሺ 292 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በክልሉ በመጀመሪያው ዙር 6 መቶ 89 የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን በዛሬው ዕለት በተጀመረው በሁለተኛው ዙር ፈተና 6 መቶ 8 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለፈተና ተቀምጠዋል።
0 Comments