ሪፎርሙ የክልሉ ፖሊስ ከነበሩበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተላቆ የፀጥታና የህግ ማስከበር ስራዎች በብቃት እንዲፈፅም አስችሏል- አቶ ኦርዲን በድሪ
በፍትህ ተቋማት የተደረገው ሪፎርም በተለይም የክልሉ ፖሊስ ከነበሩበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተላቆ የፀጥታና የህግ ማስከበር ስራዎች በብቃት እንዲፈፅም አስችሏል ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የሚገኙ የጸጥታ ተቋማት 116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በከተማው የጽዳት ዘመቻ እና አረንጓዴ ስፍራዎች እንክብካቤ ማካሄዳቸውን ገለፀዋል።
የሪፎርሙ አንዱ አካል የሆነው የተቋም ግንባታ ስራችን ብቁ፣ ገለልተኛ እና ዘመኑን የዋጀ የፀጥታ ተቋም ከመገንባት አንፃር አበረታች ውጤት እያስገኘ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
“በተለይም የክልላችን ፖሊስ ከነበሩበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተላቆ የፀጥታ እና የህግ ማስከበር ስራዎችን በብቃት ከመፈፀም ባለፈ በዚህ አይነት የልማት ስራዎች መሳየተፉ የሰራዊቱን ህዝባዊነት የሚያመላክት ነው”።
በቀጣይም የተቋም ግንባታ ስራዎችን ለማጠናከር አስፈላጊውን እገዛ እንደሚደረግ ገልፀው እለቱ በተካሄደው የልማት ስራ ለተሳየፉ የፀጥታ አመራሮችና አባላት ምስጋና አቅርበዋል


0 Comments