Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀረር ከተማ በክረምት በበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር ያስገነባቸውን 5 ቤቶች አስመረቀ

ሀረር ሰኔ 27/2016(ሀክመኮ) :- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሀረር ከተማ በክረምት በበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር ያስገነባቸውን 5 ቤቶች በዛሬው ዕለት አስመረቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በገራድ ድርጅት ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ በ2015 የክረምት በበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር የተገነቡ የአቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለነዋሪዎች ተላልፈው ተሰጥተዋል።

ቤቶቹን መርቀው ለነዋሪው እንዲተላለፍ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያና በበኩላቸው በብልፅግና ፓርቲ  ያለንን በማካፈል በወንድማማችነት የመኖር የአብሮነተ አቅጣጫን መሰረት ያደረጉ የበጎ ፈቃድ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለተጠቃሚዎች የተላለፉ የአቅመ ደካማ ዜጎች የመኖሪያ ቤቶች እድሳት እና ግንባታም ገራድ ድርጅትን በማስተባበር የተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የተጀመሩ አብሮነት እና ወንድማማችነትን ይበልጥ የሚያፀኑ እና የሚያጎለብቱ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመርሀ ግብሩ የፌዴራል ብሎም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የገራድ ድርጅት ባለቤት እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish