ሙዚየሙን መጎብኘታችን የሀገራችንን ታሪክ በአዲስ ለመመልከት ዕድል ፈጥሮልናል:- የሀረሪ ዳያስፖራ አባላት
ሀረር ሀምሌ 16/2016(ሀክመኮ):- የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየምን መጎብኘታቸው የሀገራቸውን ታሪክ በአዲስ ለመመልከት ዕድል የፈጠረላቸው መሆኑን የሀረሪ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ገለፁ።
በ26ኛው ዓለም አቀፉ የሐረር ቀን ለመሳተፍ ወደ ትውልድ አገራቸው የተመለሱ የሀረሪ ዳያስፖራ አባላት በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎትና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪነት የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የዳያስፖራ አባላቱ የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየምን መጎብኘታቸው የአገራቸውን ታሪክ በአዲስ ለመመልከት ዕድል የፈጠረላቸው መሆኑን ገልፀዋል።
የዳያስፖራ አባላቱ በከተማው ተግባራዊ የተደረገውን የኮሪደር ልማትም የተመለከቱ ሲሆን በአገሪቱ እየተከናወነ የሚገኙ የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀዋል ።
በተለይ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የአገሪቱን ገፅታ የቀየረ እና ውበትን ያላበሰ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአገሪቱ የተከናወኑ የልማት ስራዎች በሌሎች አገር ተመልክተው በአገራችን ቢኖር ብለው ሲመኙት የነበረ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአገሪቱ ያለውን የሰላም ሁኔታ ጨምሮ ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የልማት ስራዎችንም በማስተዋወቅ የቡኩላቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ የዳያስፖራ አባላቱ ገልፀዋል።



0 Comments