መስተዳድር ምክር ቤቱ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተያዘላቸው ግዜ እንዲጠናቀቁ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀመጠ
ሐረር፣ግንቦት 21/2017(ሐክመኮ):-የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በሂደት ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተያዘላቸው ግዜ እንዲጠናቀቁ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀመጠ።
መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የሚገኙበትን ደረጃ ገምግሟል።
በግምገማውም ፕሮጀክቶቹ የሚጀኙበትን ደረጃ በተመለከተ ለመስተዳድር ምክር ቤቱ ሪፖርት ቀርቦ አዝጋሚ ፍጥነት ያላቸው ፕሮጀክቶች በልዩ ሁኔታ ተገምግመዋል።
የመስተዳድር ምክር ቤቱ ፕሮጀክቶቹ በሚከናወኑባቸው አካባቢዎች በአካል በመገኘትም በተግባር ያሉበትን ደረጅ ተመልክቷል።
እየተከናወኑ የሚገኙ የኮረደር ልማቶች በተያዘላቸው ግዜ እንዲጠናቀቁ ርብርብ እንዲደረግም አቅጣጫ አስቀምጧል።

0 Comments