Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

“ሐረር ከተማን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ አበረታች ስራዎች ተከናውነዋል”-የክልሉ ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

ሀረር ሀምሌ 15/2016(ሀክመኮ):-የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ በቢሮው ባለፍት በ2016 በጀት አመት በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ተጥተዋል።

የቢሮው ኃላፊው በሰጡት መግለጫ ሐረር ከተማን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እንዲሁም ለቱሪስቶች አመቺ እንድትሆን የተለያዩ ሥራዎች መከናወኑን ተናግረዋል።

በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ልማት ስራዎች የ ጀጎልን ታሪክ፣ ባህልና እሴትን በጠበቀ መልኩ መሰራቱን ጠቁመዋል።

የቱሪስት ልማት ሥራው የአካባቢውን ማህበረሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በተለይ “ከመደመር ትውልድ” መፅሐፍ ሽያጭ እና ከክልሉ መንግስት በተመደበ በጀት የሀረር ኢኮ ፓርክ ፕሮጀክት ግንባታ ተመርቆ የጅብ ትርዒት ማሳያ ቦታ ወደ ፓርኩ ተዛውሮ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል።

“ሹዋሊድ” ክብረ በአል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ ማስመዝገብ መቻሉን የገለጹት የቢሮ ኃላፊው ዘንድሮም በአሉ ባማረና በደመቀ መልኩ መከበር መቻሉን ተናግረዋል።

የክልሉን ባህል ፣ ቅርስና ቱሪዝም ከማስተዋወቅ አንጻር ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወኑን ገልጽው በተለይም ከተማዋ ሙዚዬሞችን ያቀፈች በመሆኑ የቱሪዝም ሎጎ ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱን ነው ያስረዱት፡፡

በክልሉ የህዝብን አብሮነትና አንድነትን የሚያጎለብቱ እንዲሁም ሕብረ ብሄራዊ አንድነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ስራዎች መከናወኑን ገልጸዋል።

በ2016 የበጀት አመት ጉዳት የደረሰባቸው 14 ባህላዊ ቤቶች እና 4 ጥንታዊ አድባራት ይዘታቸውን በጠበቀ መልኩ የማደስ ስራ መሰራቱን የገለጹት አቶ ተወለዳ በተጨማሪም የሱቅጣጥ በሪ ታሪካዊ በር እድሳት ግንባታ መጠናቁቁን ጠቁመዋል ::

ባለፈው የበጀት አመት ክልሉን የጎበኙ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች 100 % እንዲሁም የውጪ ቱሪስቶች 24 % ብልጫ ማሳየቱን አክለው ገልጸዋል።

በክልሉ የቱሪስት ልማት ሥራው የአካባቢውን ማህበረሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንደሚከናወን በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish