Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ሐረር ከተማን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ውጤት አስገኝተዋል

ሐረር ከተማን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት ማስገኘታቸውን የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

በክልሉ ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ዳይክተር አቶ ሳሚ አብዱልዋስዕ እንደተናገሩት በተያዘው የበጀት አመቱ እስካሁን በተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ሐረር ያሏትን እምቅ የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋልና ህዝብን ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።

ቅርሶችን ከማልማትና ጠብቆ በማቆየት አንፃር በተለይም ከለውጡ ወዲህ የክልሉ አመራር ቁርጠኛ አቋም በመያዝ የተለያዩ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ ስራዎች ተሰርተዋል።

እነኚህ ስራዎችም ቅርስን ጠብቆ ለትውልድ ከማስተላለፍ ባሻገር የክልሉን ገቢ እንዲያድግና የአሁኑ ተውልድ በዘርፉ ያለው ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማትም ዘርፉን በማነቃቃት ረገድ ጉልህ ድርሻ እያበረከተ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።

በመጀመሪያው ሩብ አመቱም በተለያዩ አግባቦች ክልሉን የቱሪዝም ዘርፍ የማስተዋወቅና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል

በአጠቃላይ በመጀመሪያው ሩብ አመት 2893 የውጭና 46739 የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ክልሉን እንደጎበኙ ገልጸዋል።

በቀጣይም ሐረር ከተማን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችና የተገኙ ተጨባጭ ውጤት የበለጠ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ነው የተናገሩት።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish