ለ9 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቅርጫት ኳስ ውድድር በሀረር አሸናፊነት ተጠናቀቀ
ሀረር ሀምሌ 7/2016(ሀክመኮ):-በሀረር ከተማ 26ተኛውን አለም አቀፉ የሀረር ቀን በማስመልከት ሲካሄድ የቆየው የቅርጫት ኳስ ውድድር በሀረር የቅርጫት ኳስ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቋል።
26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀንን ምክንያት በማድረግ በሀረር ከተማ ሲካሄድ የቆየው የቅርጫት ኳስ ውድድር በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
ዛሬ በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ ከድሬደዋ ከተማ ጋር የተደረገው የሀረር ቅርጫት ኳስ ቡድን 47 ለ 38 በሆነ ውጤት ድሬደዋን በማሸነፍ ዋንጫ አንስቷል።
ውድድሩ ዲያስፖራዎችን ጨምሮ 7 ቡድኖች የተሳተፉበት ሲሆን በመርሀግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ያሲን ዩሱፍን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።






0 Comments