ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተነሱ ጥያቄዎች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች እየቀረበላቸው ይገኛል። ከተነሱላችው ጥያቄዎች መካከል፥
◾️ጦርነት ሰባኪ አካላት ተፈጥረዋል፤ በዚህ ረገድ እነዚህ አጥፊ ሃሳብ ያላቸው አካላት ኢትዮጵያን ችግር ውስጥ እያስገቡ በመሆኑ መንግስት ይህን ለማስቆም ምን ሰርቷል?
◾️አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባትና ድህነትን ያሸነፈች ኢትዮጵያን ወደታለመው ግብ ለማድረስ የመሐል ዘመን ወጥመድ ማለፍ ይገባል፤ እነዚህ ፈተናዎችስ ምንድን ናቸው?
◾️የመንግስት ሠራተኛውን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል አኳያ መንግስት ምን አይነት ሥራዎችን ለማከናወን አስቧል? የከተሞችን የቤት አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ምን እየተሰራ ይገኛል?
◾️የሀገራዊ ምክክር ወሳኝ ሥራ በትግራይ ክልል እንዲከናወንና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያውያንን ውጤት እንዲያመጣ ከማን ምን ይጠበቃል?
◾️መንግስት ከበፊቱ የተሻለ ሰላም እያመጣሁ ነው ይላል ማሳያዎቹ ምንድን ናቸው፤ በሰላምና ፀጥታ ላይ የተሰሩ ሥራዎችስ ምን ምን ናችው?
◾️ሙስና ሕዝቡን እያማረረ ነው በዚህ ረገድ ሙስናን ለመከላከል ምን እየተሰራ ነው?
ጥያቄዎቹ እንደቀጠሉ ናቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጥያቄዎቹ መልስ እንዲሁም የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም በተመለከተ ማብራሪያ የሚሰጡ ሲሆን፤ የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትም ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

0 Comments