ለኮሪደር ልማቱ ውጤታማነት ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ በሀረሪ ክልል የተለያዩ የገጠር ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ
በሀረሪ ክልል የተጀመረው የገጠር ኮሪደር ልማት ውጤታማ እንዲሆን ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት የኮሪደር ልማት ስራው ዜጎች የተሻለ አካባቢን በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ የላቀ ነው ብለዋል።
በተለይም በገጠሩ አካባቢ የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች አርሶ አደሩን የአኗኗር ዘዬ እንዲቀየር ሚናው የላቀ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኮሪደር ልማቱ በተለይም በገጠሩ አካባቢ የመንገድ መሰረተ ልማት እንዲሟላ በማስቻል አርሶ አደሩ ምርቱን ከእንግልት ነፃ በሆነ መልኩ ወደ ገበያ እንዲያቀርብ ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ሰፋፊ የእግረኛ መንገድ እንዲኖር በማድረግ የትራፊቅ አደጋ እንዲቀንስ እገዛ ያደርጋልም ብለዋል።
ለኮሪደር ልማቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ለስኬታማነቱ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል።
በክልሉ በሚገኙ ሦስት የገጠር ወረዳዎች አዳዲስ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ይታወሳል።



0 Comments