Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ህዝቡ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በማካሄድ የዕድሉ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል- ነዋሪዎች

በሀረሪ ክልል በየአካባቢው እየተሰጠ በሚገኘው የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎት ህዝቡ የዕድሉ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል ሲሉ የአገልግሎት ተጠቃሚ ነዋሪዎች ተናገሩ 

በክልሉ በየማዕከላቱ ምዝገባ ሲያካሄዱ  ያገኘናቸው ነዋሪዎች እንዳሉት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እንደሀገርና ግለሰብ የሚያስገኘው ፋይዳ የላቀ ነው።

በምዝገባ ሂደት ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን በተግባር መመልከታቸውን ጠቁመው ህዝቡም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፋይዳን በመገንዘብ ተጠቃሚ መሆን ይገባል ሲሉ ነው የተናገሩት።

የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ በተለይም የሀገርን እና የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ጠቁመዋል።

በክልሉ ሁሉም በሚገኙ ሁሉም የገጠርና ከተማ ወረዳዎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እየተከናወነ ይገኛል።

#DigitalID #Fayda #InclusiveID #ፋይዳለኢትዮጵያ

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish