26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ያለምንም የፀጥታ ችግር ለማክበር የሚያስችል ዝግጅች ተደርጓል- የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
ከነገ ጀምሮ በሀረር ከተማ የሚከበረው 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ካለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በፀጥታው ረገድ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከማስቻል አንፃር አስፈላጊው የዝግጅት ስራ ተጠናቋል።
ከአጋዥ የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተለይም የምስራቅ ቀጠና የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ጋር በመቀናጀት በቂ የቅድመ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል።
በተለይም ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በዓሉ የተሳካ እንዲሆንና በክልሉ እየታየ የሚገኘው አንፃራዊ ሰላም ቀጣይነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅትም በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል።
በመሆኑም በተለይም ሰላም ወዳዱ የክልሉ ህዝብ እንደወትሮው የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅና የበዓሉ አከባበር ስኬታማ እንዲሆን ሚናውን እንዲወጣ ጠይቀዋል ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን

0 Comments