Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

2017 ዓመት የትጋትና የስኬት ዓመት ነው – አቶ ጌቱ ወዬሳ

በሀረሪ ክልል የፓርቲ እና የመንግስት የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም እስከ ወረዳ ያሉ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንዳሉት የግምገማ መድረኩ የ2017 ማጠቃለያና በ 2018 ዋና ዋና አቅጣጫዎች ላይ ውይይት የሚደረግበት ነው።

በዚህም መሰረት በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት ከተቀመጠላቸው ራዕይ፣ግብና አላማ አንፃር የሚገመገሙ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይ የአገልግሎት አሰጣጥን በመገምገም የተመዘገቡ ውጤቶችን ይበልጥ ለማሻሻልና ያልተሻገርናቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በቀጣይ ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።

የትርክት የበላይነትን ከማስረፅ አንፃር የተከናወኑ ተግባራትም በጥልቀት እንደሚገመገሙ ነው የጠቆሙት።

በ2017 በጀት አመት ለማሳካት በዕቅድ የተያዙ የተግባር አፈጻጸም ረገድ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ህዝቡን በማሳተፍ በተቀናጀ መንገድ መስራት በመቻሉ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም መስፈን እንደቻለ ተናግረዋል።

በንቅናቄ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ያወሱት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ፥ ከተረጂነት ለመውጣት የተከናወኑ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀዋል።

ገዥ ትርክትና ቅቡልነት እንዲረጋገጥ በመሰራቱ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ አዎንታዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

አባልና አመራሩ በፓርቲው እሳቤዎችና አቋሞች ላይ የጠራ ግንዛቤና አመለካከት እንዲኖራቸው በማድረግ ረገድ አበረታች ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ እና አምስተኛ ዓመት ምስረታ በዓል በተቀናጀና በተናበበ መንገድ መሳካት ችሏል ነው ያሉት።

አመራሩ የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራትን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ድሎችን ማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በመቅረፍ ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ ህዝብን በማሳተፍ መስራት ይገባል ብለዋል።

ዛሬ የተጀመረው የግምገማ መድረክ እስከ ነገ ድረስ እንደሚቀጥል ከወጣው መርሃግብር ለማወቅ ተችላል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ፣የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድን ጨምሮ የክልሉ የመንግስትና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ ዓመራሮች እየተሳተፉ ነው።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo