Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የኮሪደር ልማቱ ዘመናዊ ከተማን ከመፍጠር ባሻገር ከተማዋን ለኑሮ ምቹ አድርጓል

ሀረር ነሀሴ 24/2017(ሀክመኮ):-የሀረር ከተማ የኮሪደር ልማት ዘመናዊ ከተማን ከመፍጠር ባሻገር ከተማዋን ለኑሮ ምቹ እንድትሆን ማስቻሉን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች ገለፁ።

የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አመራሮች፣የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ እና የክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በሀረር ከተማ የተከናወኑ እና በሂደት ላይ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።

አመራሮቹ በመስክ ምልከታው ላይ እንደገለፁት እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ዕድገት ከማፋጠን ባለፈ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው።

በተለይ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ስራ አለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ፅዱና ውብ ገፅታን እንዲላበስ ያስቻለ ሆኖ እንዳገኙት ገልፀዋል።

የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ስራ ቅርሱን ወደ ምቹ የመኖሪያ አካባቢነት የቀየረና ቅርሱን ምቹና ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ ያስቻለ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በቅርሱ ውስጥ የተከናወነው የመልሶ ልማት ቅርሱ ህያውነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ያስቻለ መሆኑንም አክለዋል።

በቅርሱ ውጫዊ ክፍል የተገነቡ የህዝብ መናፈሸዎች ቅርሱ ተጨማሪ ውበት እንዲጎናፀፍ ያስቻሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በከተማው ተግባራዊ የተደረገው የኮሪደር ልማት በብርሃን የተሞሉ ሰፋፊና ምቹ የእግረኛ፣የተሽከርካሪ፣የሳይክል መንገዶችን፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን፣የህዝብ መናፈሻዎችን በመፍጠር የከተማዋን የቀድሞ ገፅታ የቀየረ መሆኑን አክለዋል።

በከተማው እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሲጠናቀቅ የሀረር ከተማን ለነዋሪዎቿ ይበልጥ የተመቸች፤ቱሪስቶች መርጠዋት የሚጎበኟትና ረጅም ጊዜ የሚቆዩቧት፣ ሳቢና ማራኪ ከተማ ያደርጋታልም ብለዋል።

አመራሮቹ በክልሉ የሚገኙ የሰላም አደረጃጀቶችና በክረምት በጎ ፈቃድ የታደሱና የተገነቡ የአቅም ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤቶችንም በወረዳዎች በመገኘት ተመልክተዋል።

አመራሮቹ ከመደመር ትወልድ ሽያጭ በተገኘው ገቢ እና በክልሉ መንግሥት በተመደበ በጀት የተገነባውን የሐረሪ ኢኮ ቱሪዝም ፓርክ የተመለከቱ ሲሆን ፓርኩ ለጎብኚዎች በሚያመች መልኩ መገንባቱ ዘርፉን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ የሚያበረክት ነው ብለዋል።

AbadirPlaza #Hararjugol #corridordevelopment #hararekopark #ሐረርኮሪደር #Peace #News #ዜና

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo