Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ተግባራዊ በማድረግ ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ተግባራዊ በማድረግ ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳደሩ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት በመንግስት ተቋማት በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎችን ለምሬት የዳረጉ አገልግሎቶችን በመፈተሽ ለማስተካከል እየተሰራ ነው።

በዚህም በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በየፈርጃቸው በአንድ ማዕከል በማስተሳሰርና ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ከአድልዎ የፀዳ፤ ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ጥራት ያለውና ጊዜ ቆጣቢ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቷል።

የተገልጋዮች እርካታን ለማሳደግም በክልሉ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስጀመር ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo