የሀረርን የማንሰራራት ዘመን ለማስቀጥል እና ለማፋጠን አቅም የሚሆን ተሞክሮ ከእየሩሳሌም ከተማ አግኝተናል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ
ሀረር፣መስከረም 13/2018(ሀክመኮ):-የሀረርን የማንሰራራት ዘመን ለማስቀጥል እና ለማፋጠን አቅም የሚሆን ተሞክሮ ከእየሩሳሌም ከተማ ማግኘታቸውን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለፁት ሀረር እና እየሩሳሌም በመንፈሳዊም ሆነ ቁሳዊ ጉዳዮች በብዙ መልኩ ተመሳሳይ ናቸው።
በቆይታችን ለክልላችን ኢኮኖሚ አድገት ጠቀሚ የሆኑ የቱርዝም፣ የቅርስ ጥበቃ እና የኮሪደር ልማት ስራዎችን የበለጠ የሚያጠናክሩ፣ ቁጭት የሚፈጥሩና የስራ ተነሳሽነትን የሚጨምሩ ግብአቶችን አግኝተናል ብለዋል።
ለዚህ ተሞክሮ ስኬት ከሀሳብ ጀምሮ እስከ ክትትልና ድጋፍ እገዛ ላደረጉ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋና በማቅረብ በጉብኝቱ ያገኙትን ተሞክሮ በአጭር ጊዜ ወደ ተግባር ለመቀየር እንደሚሰሩም ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።



0 Comments